ትግላችን: የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ (Our Struggle: The Story of the Ethiopian People's Revolutionary Struggle)
Book information
Description
“የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ከተቀጣጠለበት እስከ ተቀለበሰበት ድረስ ያለው ጊዜ ከመሰል ሕዝባዊ አብዮቶች ጋር ስናነፃፅረው በለጋና በአጭር የተቀጨ አብዮት ቢሆንም በአሥራ ሰባት ዓመታት ውስጥ ያደረገውን ፈጣን ጉዞ፣ ያስተናገዳቸውን ሕዝባዊ ተግባሮች፣ የገጠሙትን ፈተናዎችና የጠየቁትን መስዋዕትነት በሦስት ተከታታይ ቅፆች ለማቅረብ ተገድጃለሁ። የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ መሪ ግለሰቦች የሚመጡና የሚሄዱ አላፊዎች ሲሆኑ ሃገርና ሕዝብ ግን ዘላለማዊ ናቸው። ይህም ቢሆን በአንድ ታሪካዊ ወቅት መንግሥታት፣ የፖለቲካ ደርጅቶች ወይም ግለሰቦች ያከናወኗቸው ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተግባሮች ማንም ወደደ ጠላ የዚያ ሃገርና ሕዝብ ታሪክ ናቸው። ትግላችን ስሙ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ አንድ ትውልድ በሙሉ ቀፎው እንደተነካበት የንብ ሠራዊት ተቆጥቶ በመነሳት ገበሬው ከገባርነት፣ የሠራተኛውን መደብ ከምንዳ ባርነት፣ ጠቅላላውን ባተሌ ሠርቶአደር ሕዝብ ከድንቁርና አረንቋና እጅግ አሳፋሪ ከሆነ የዘላለም ድህነት መንጥቆ በማውጣት ራሱንና አገሩን ለመለወጥ በጀመረው ትግል መሪር መስዋዕትነትን ከፍሎ የትግሉን ጣፋጭ ፍሬ ሳይቀምስ፣ አንድነቱንና ሰላሙን ሳያገኝ እንደገና የጨለመበት አሳዛኝ ሕዝብ ልሳን እንጂ አንባቢን በደስታ ለመመሰጥ የተዘጋጀ የሥነፅሁፍ ድግስ አይደለም። በአብዮት የትግል ጎራ ወይም አሰላለፍ ላይ ብቻ በማተኮር፣ በብቀላ፣ የአጥቂነት ወይም የተከላካይነት ስሜት አጥቅቶኝ በማጋነን ወይም በማቃለል ታሪኩን ላለማዛባት በተቻለኝ መጠን ከራሴ ጋር ታግያለሁ፣ ከህሊናዬም ጋር ተሟግቻለሁ። ይኸ ትግላችን የተሰኘ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ታሪክ ትምህርት በመስጠቱ ረገድ ስለሚኖረው ፋይዳ ፍርዱን ለአንባቢው እተዋለሁ።” ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ፕሬዝዳንት ምስጋና የአሳታሚው ማስታወሻ መቅድም መግቢያ -ጥንታዊት ኢትዮጵያ -የአክሱማውያን መንግሥትና ሥልጣኔ አነሳስ -ኢትዮጵያ በመካከለኛው ዘመን: የአክሱም መንገሥት ፍፃሜና የዛጉዌ መንግሥት አነሳስ -ከዛጉዌ በኋላ የመጡ ሥርወ መንግሥታት የጠበቃቸው ሥራና የገጠሟቸው ፈተናዎች -ኢማም አህመድ ግራኝ የመራው አመፅ፣ የእስላም አገርችና የፖርቹጋሎች በኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መገባች -የኦርሞ ማህበረሰብ ፈለሳና ወረራ -የሥርዓተ አልበኛች መሣፍንት ዘመን -ዘመነ ኢምፔሪያሊዝም -የአውሮፓ የቅኝ ገዛት ኃይሎችና የአካባቢው ባዕዳን ተስፋፊዎች በኢትዮጵያ ላይ ያደረጓቸው ከበባዎችና ብሎም ወረራዎች -የቱርኮች ከበባና ወረራ -የግብፅ መንገሥት ያደረገው ከበባና የሰነዘረው ወረራ -የአውርፓ መንግሥታት ገብፆችን ተከተው በኢትዮጵያ ላይ ያደረጉት ከበባና ወረራ -የኢጣሊያ መንግሥት ወረራ -ድህረ ፋሽስት ኢትዮጵያ -የኢትዮጵያውያን ጀግንነትና አይበገሬ አርበኝነት I. ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት መቃረቢያ፣ ዋዜማና አጥቢያ 1. የአብዮቱ መቃረቢያ 2. የአብዮቱ ዋዜማ 3. የአብዮቱ አጥብያ II. አብዮታዊት ኢትዮጵያ፡ ከትግል ወደ ድል፣ ከድል ወደ ትግል የኢትዮጵያ አብዮተኞች ጉዞ 4. የአብዮቱ ሟማግሥት 5. ደርግና የልጅ እንዳልካቸው መንገሥት 6. ደርግ ከልጅ ሚካኤል እምሩ መንገሥት ጋር 7. ዘውዱን ለመገርሰስ የተደረጉ የመጨረሻ ዝገጅጀቶች 8. ደርገና ሌ/ጄነራል አማን ሚካኤል አንዶም 9. ደርገና ቫለቃ ተፈራ ተከለዓብ 10. ደርግና ሌ/ኮሎኔል አዋናሩፋ አባተ 11. ደርግና አፄ ኃይለሥላሴ 12. የጉልታዊውን ሥርዓተ ማሀበር ላዕላይና ታሀታይ መዋቅር ስለማፈራረስ III. መሬት ለአራሹ 13. የገጠሩን የእርቫ መሬት የአርሶ አደሩ ይዞታ የሚያደርገው አዋጅ ጥናትና መሰናዶ 14. እድገት በሕብረት የእውቀትና የሥራ ዘመቻ 15. የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ገበሬዎች የቀበሌ ማህበር ወደ ከፍተኛ ንቃት፣ ድርጅት፣ ምርትና ማህበራዊ ይዞታ የማሸጋገር እምርታ IV. የሠራተኛው መደብና የኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ አደረጃጀት 16. የኢትዮጵያ ሠራተኞች መተዳደሪያ ሕግ 17. የሠራተኛው ማህበርና የኢንዱስትሪው ከፍለ ኢኮኖሚ አደረጃጀት 18. በአብዮታዊት ኢትዮጵያ የእደ ጥበብ ኢንዱስትሪ V. በአብዮታዊት ኢትዮጵያ ለሰላም የተደረጉ ጥረቶች 19. አብዮታዊት ኢትዮጵያን ለማዳን አማራጭ የሌለው መድኃኒት 20. ድህረ አብዮት ኢትዮጵያ የሰላም ጥረት በኢትዮጵያዊያን መካከል 21. ለኤርትራ ክፍለ ሃገር ችግር ሰለማዊ መፍትሄ ለማግኘት የተደረጉ ጥረቶች 22. ከሶማሊያ ተስፋፊ መንግሥት ጋር ወደ ጦርነት ላለማምራት በድህረ አብዮት ኢትየጵያ የተደረጉ የሰላም ጥረቶች VI. የውጭ ጥቃቶች 23. ከውጭ የተሠነዘሩብን ጥቃቶች አብዛኛዎቹ በጠላቶቻችን ብርታት ሳይሆን በኛ ድክመትና የዋሀነች ንሙ 24. በዳግማዊ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት 25. በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት 26. በአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት VII. ሃገርንና አብዮትን የማዳን ጦርነት ዝግጅት 27. የታጠቅ ጦር ሰፈር ምስረታ 28. የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት አመሰራረት 29. ሕዝባዊ ሠራዊታችንን ለማስታጠቅ የተደረጉ ጥረቶች 30. የአብዮታዊ የመከላከያ ሠራዊት አስተዳደር 31. የአብዮታዊ የመከላከያ ሠራዊት አደረጃጀት 32. ዓለም ያደነቀው የኢትዮጵያ አብዮታዊ የመከላከያ ሠራዊት ሰልፍ VIII. ሃገርንና አብዮትን የማዳን ፍልሚያ 33. የሶማሊያን መንግሥት ወራሪ ሠራዊት ጥቃት ለመከላከል በምሥራቅና በደቡብ ግምባር አብዮታዊ ሠራዊታችን ያደረገው ትግል 34. በሐረርጌ፣ በባሌና በሲዳሞ ከፍላተሃገር ደጋማ አውራጃዎች ለሰባት ወራት የተደረገ የመከላከል ትግል 35. ከሞስኮ ስንመለስ በአገራችን የጠበቁን ሁኔታዎች 36. የኢሕአፓ አደገና ሴራ በቆሬ የጦር ግምባር IX. ከመከላከል ወደ ማጥቃት 37. ለመልሶ ማጥቃት ውጊያ የተደረጉ መሰናዶዎች 38. ወራሪው የሶማሊያ መንግሥት የጦር ኃይል ሐረርጌን ለመያዝ ያደረገው የመጨረሻ ጥረት 39. የኢትዮጵያ አብዮታዊ ሠራዊት ከመከላከል ወደ ማጥቃት መሸጋገር X. ማጠቃለያ 40. ያሸነፈው አብዮት ነው! መዘርዝር -ከየካቲት 1966 ዓ.ም እስከ መስከረም 1967 ዓ.ም -ከመስከረም 1967 ዓ.ም እስከ መስከረም 1968 ዓ.ም -ከመስከረም 1968 ዓ.ም እስከ መስከረም 1969 ዓ.ም -ከመስከረም 2969 ዓ.ም እስከ መስከረም 1970 ዓ.ም የቃላቶች ትርጉም ዋቢ መጻሕፍት መጠቁም
Similar books
ትግላችን: የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ, ቅጽ.2 (Our Struggle: The Story of the Ethiopian People's Revolutionary Struggle, Volume 2)
2016 · PDF
መጽሐፍ ቅዱስ
1993 · PDF
ጋቢና ዋራንት: የቀይ ሽብር እስር ከሶደሬ እሰከ ከርቸሌ
2006 · PDF
የአስመራ ማኒፌስቶ
1974 · PDF
Tinsae Mahlet
2005 · PDF
Metsehafe Getsawe
ምስክርነት (በባለስልጣናቱ አንደበት) (Testimony in the Words of the Authorities)
2015 · PDF
ከኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማሪያም አንደበት: በኢትዮጵያ ላይ የተሸረቡ ሴራዎች እና ኢትዮጵያውያን የፈፀሙት ታላቅ ስህተት (From Col. Mengistu Haile Mariam's Mouth: Conspiracies Against Ethiopia and the Great Mistake Made by Ethiopians)
2015 · PDF